አቶ ትግስቱ አወሉ ራሳቸውን ከፌዴራሊስት ሃይሎች ፎረም አገለሉ | OROMIYAA TIMES
Skip to toolbar

አቶ ትግስቱ አወሉ ራሳቸውን ከፌዴራሊስት ሃይሎች ፎረም አገለሉ

አቶ ትግስቱ አወሉ ራሳቸውን ከፌዴራሊስት ሃይሎች ፎረም አገለሉ

የአቶ ትግስቱ አወሉ ፎቶ ከኢፕድ የተወሰደ

አቶ ትግስቱ አወሉ ከፌዴራሊስት ሃይሎች ፎረም ራሳቸውን ማግለላቸወን አስታወቁ።

አቶ ትግስቱ ዛሬ በሰጡት መግለጫ እንደተናገሩት፤ የፌዴራሊስት ሃይሎች በሚል የተሰባሰበው ሃይል ህወሓት ዳግም የበላይነቱን ለመመለስ የሚያደርገው ጥረት አካል ነው።

እንደ አቶ ትግስቱ ገለጻም፤ ይህ ፎረም የኢትዮጵያን ህዝብ ዳግም ለማስለቀስ ያለመ ነው።

ህወሓት የብልጽግና ፓርቲ አሃዳዊ ነው የሚለው የብሄር ብሄረሰቦችን ቀልብ ለመሳብና የስብስቡ አካል ለማድረግ ነው ያሉት አቶ ትግስቱ፤ የፎረሙ አላማና አካሄድ የህወሓትን የበላይነት ለመመለስ ያለመ በመሆኑ ራሳቸውን ከፎረሙ ምክትል ሰብሳቢነት ጭምር ማግለላቸውን አስታውቀዋል።

ዝርዝሩን ይዘን እንመለሳለን።

ምንጭ: ኢፕድ

Leave a Comment

Your email address will not be published. Required fields are marked *