የከፍተኛ የመንግስት ስራ ሃላፊዎች ምደባ ከብሄርና ከማግለል ጋር አይገናኝም -ኢ.ፕ.ድ | OROMIYAA TIMES
Skip to toolbar

የከፍተኛ የመንግስት ስራ ሃላፊዎች ምደባ ከብሄርና ከማግለል ጋር አይገናኝም -ኢ.ፕ.ድ

የከፍተኛ የመንግስት ስራ ሃላፊዎች ምደባ ከብሄርና ከማግለል ጋር አይገናኝም -ኢ.ፕ.ድ

የከፍተኛ የመንግስት ስራ ሃላፊዎች ምደባ ከብሄርና ከማግለል ጋር እንደማይገናኝ የብልፅግና ፓርቲ አስታወቀ።

ፓርቲው ከሰሞኑ የጠቅላይ ሚኒስትር ጽ/ቤት በተለያዩ የስራ መደቦች ላይ በሚኒስትር ደረጃ ሽግሽግና አዳዲስ ሹመቶችን የመስጠት ስራ ማካሄዱን አስታውሷል።

ይህም የተለመደና ለስራ ቅልጥፍና የተሸለ አፈጻጸም ለማረጋገጥ ሲባል በየጊዜው የሚከናወን ስራ ነው ያለው ፓርቲው የአሁኑም እንደተለመደው መንግስት የስራ አፈጻጸምን፤ ብቃትንና ሲታዩ የነበሩ ጉድለቶችን ማረም እንዲሁም የስራ አፈጻጸም ጉድለት ያለባቸውን በሌላ መተካትን መሰረት ያደረገ ሽግሽግ ነው፤ አዳዲስ ሹመቶችም ተሰጥተዋል።

በመሆኑም ከዚህ ጋር ተያየዞ አንድን ብሄር ለማግለልና ከስራ ለማፈናቀል የተደረገ አድርጎ የሚያቀርቡ አካላት አለማቸው ለነገሮች የተሳሳተ ትሩጋሜ በመስጠት ህዝብን ማደናገር መሆኑን ማስገንዘብ እንደሚፈልግ ከፓርቲው ያገኘነው መረጃ ያመለክታል።

Leave a Reply

Your email address will not be published. Required fields are marked *