በኢትዮጵያ የሰብአዊ እርዳታ ምላሽ ለማድረግ አንድ ቢሊየን ዶላር እንደሚያስፈልግ የተመድ ገለጸ | OROMIYAA TIMES
Skip to toolbar

በኢትዮጵያ የሰብአዊ እርዳታ ምላሽ ለማድረግ አንድ ቢሊየን ዶላር እንደሚያስፈልግ የተመድ ገለጸ

በኢትዮጵያ የሰብአዊ እርዳታ ምላሽ ለማድረግ አንድ ቢሊየን ዶላር እንደሚያስፈልግ የተመድ ገለጸ።


እ.ኤ.አ በ2020 በኢትዮጵያ የሰብአዊ እርዳታ ምላሽ ለመስጠት እንዲያስችል የአንድ ቢሊየን የአሜሪካ ዶላር እንደሚያስፈልግ የተባበሩት መንግሥታት ድርጅት፣ የኢትዮጵያ መንግሥት እና አጋር አካላት ይፋ ማድረጋቸውን የድርጅቱ ቃል አቀባይ ስቴፈን ዱጄሪክ አስታወቁ፡፡

በኢትዮጵያ ሰብአዊ እርዳታ ለማድረግ እቅድ ከተያዛላቸው 8 ነጥብ 4 ሚሊየን ሰዎች መካከል 7 ሚሊየን የሚሆኑት የሰብአዊ እርዳታ ምላሽ የሚያስፈልጋቸው መሆኑን ዱጄሪክ በጋዜጣዊ መግለጫቸው ላይ ተናግረዋል፡፡

በግጭት የተነሣ የሚደርስ መፈናቀል፣ በበሽታ ወረርሽኝ፣ በአንዳንድ አገሪቱ አካባቢዎች የሚታይ የዝናብ እጥረት እና ሌሎች ስፍራዎች ደግሞ ያለ የጎርፍ ጉዳት ሰብአዊ እርዳታ ለማድረግ መንስኤዎች መሆናቸው ተገልጿል፡፡

ኢትዮጵያ በአሁኑ ወቅት የበረኃ አንበጣ ወረርሽኝ ተጠቂ በመሆኗ ምክንያት የዜጎች የመኖር ሁኔታ እና የምግብ ዋስትና አደጋ ውስጥ መግባቱንም የተመድ በሪፖርቱ ጠቅሷል፡፡

ድርጅቱ ባለፈው ዓመት በኢትዮጵያ የሰብአዊ እርዳታ ከሚሹ 8.86 ሚሊየን ሰዎች መካከል 8 ነጥብ 3 ሚሊየን ለሚሆኑ ዜጎች የአንድ ነጥብ 314 ቢሊየን የአሜሪካን ዶላር ሰብስቦ እርዳታ ለማድረግ ሲሠራ እንደነበር በመረጃው ተጠቅሷል፡፡

Oromia Standard

Leave a Comment

Your email address will not be published. Required fields are marked *