በጋሞ ዞን ጋጮ ባባ ወረዳ ወቅቱን ባልጠበቀ ዝናብ በተከሰተ ናዳ የ4 ሠዎች ሕይወት ማለፉ ተገለፀ | OROMIYAA TIMES
Skip to toolbar

በጋሞ ዞን ጋጮ ባባ ወረዳ ወቅቱን ባልጠበቀ ዝናብ በተከሰተ ናዳ የ4 ሠዎች ሕይወት ማለፉ ተገለፀ

በጋሞ ዞን ጋጮ ባባ ወረዳ ወቅቱን ባልጠበቀ ዝናብ በተከሰተ ናዳ የ4 ሠዎች ሕይወት ማለፉ ተገለፀ
ጥር 22/2012ዓ.ም፦


የወረዳው አርሻና ተፈጥሮ ሀብት ልማት ጽ/ቤት ኃላፊ አቶ ግላ ግርማ ለጋሞ ዞን ሕዝብ ግንኙነት ጽ/ቤት እንደገለፁት ጥር 22/2012ዓ.ም በወረዳው ገፄ ቀበሌ ጧት ከ12:00 እስከ 1:00 ሰዓት በጣለ ከባድ ዝናብ በተከሰተ ናዳ 2 ወንዶችና 2 ሴቶች ሲሞቶ 2 ሴቶች ላይ ከባድ ጉዳት መድረሱን ተናግረዋል ።
በናዳው 12 የቤት እንስሳት ሲሞቱ ፣ 12 እማወራዎች እና አባወራዎች ውስጥ 46 ቤተሰብ
ከቤት ንብረታቸው የተፈናቀሉ ሲሆን 29.375 ሄ/ር ላይ ያለ ሰብል መውደሙን አቶ ግላ ተናግረዋል ።
የወረዳው ዋና አስተዳዳሪ አቶ ደረሰ ዳይሾሌ በበኩላቸው ጉዳት ለደረሰባቸው ወገኖች አስፈላጊው እርዳታ እንድደረግላቸው ጥሪ አቅርበዋል ።
የጋሞ ዞን ዋና አስተዳደር ተወካይ አቶ ደርሶ በላይ ለተጎዱ ወገኖች የሚደረገው እርዳታ በአስቸኳይ እንዲደርስ እንደሚደረግ ተናግረው ናዳው በደረሰበት አካባቢ ያሉ ወገኖች ከአከባቢውን ቶሎ ለቀው መውጣት እንዳለባቸው መልዕክታቸውን አስተላልፈዋል ።
የዞኑ ብልጽግና ፓርቲ ተወካይ አቶ እንዳልካቸው አስራት በአደጋው በሞቱና በተጎዱ ወገኖች ላይ በደረሰው ጉዳት የተሰማቸውን ሐዘን ገልጸው ለተጎጂዎች የአጭር ና የረጅም ጊዜ ዘላቂ መፍትሄ እንደሚደረግ ተናግረዋል።

ምንጭ: Gamo Zone Administration

Leave a Reply

Your email address will not be published. Required fields are marked *