ኤምባሲው በኬንያ የተለያዩ ማረሚያ ቤቶች የሚገኙ ኢትዮጵያውያን መብታቸው እንዲከበርና ወደ ሀገር ለመመለስ እየሰራ ነው | OROMIYAA TIMES
Skip to toolbar

ኤምባሲው በኬንያ የተለያዩ ማረሚያ ቤቶች የሚገኙ ኢትዮጵያውያን መብታቸው እንዲከበርና ወደ ሀገር ለመመለስ እየሰራ ነው

ኤምባሲው በኬንያ የተለያዩ ማረሚያ ቤቶች የሚገኙ ኢትዮጵያውያን መብታቸው እንዲከበርና ወደ ሀገር ለመመለስ እየሰራ ነው

ኤምባሲው በኬንያ የተለያዩ ማረሚያ ቤቶች የሚገኙ ኢትዮጵያውያን መብታቸው እንዲከበርና ለሀገራቸው ለማብቃት እየሰራ ነው።

ባለፉት ስድስት ወራት ከህገወጥ የሰዎች ዝውውር ጋር በተያያዘ 300 የሚሆኑ ዜጎችን ወደ ሀገር ቤት የመለሰ ሲሆን በተለያዩ ጥፋቶች ተፈርዶባቸው ታስረው የሚገኙትንም ለማስፈታት ጥረት እያደረገ ይገኛል።

በኬንያ የኢፌዲሪ ባለሙሉ ስልጣን አምባሳደር መለስ ዓለም በኬንያ ማረሚያ ቤቶች የሚገኙ ዜጎችን በተመለከተ ከኬንያ የማረሚያ ቤቶች አገልግሎት ኮሚነሽር ጀነራል ዋይክሊፍ ኦጋሎ (Commisssioner General Wycliffe Ogallo) ጋር ተነጋግረዋል።

ኤምባሲው የዜጎች መብት እንዲከበርና የተፈረደባቸው ወገኖቻችን ምህረት ተደርጎላቸው ለሀገራቸው እንዲበቁ ለማድረግ ከኬንያ መንግስት ባለድርሻ አካላት ጋር በቅርበት ተባብሮ እየሰራ ይገኛል።

ኮሚነሽር ጀነራል ዋይክሊፍ በበኩላቸው ኤምባሲው በማረሚያ ቤት ለሚገኙ ዜጎቹ ለሚያደርገው የቆንስላ ድጋፍ አስፈላጊው ትብብር ሁሉ ይደረጋል ብለዋል።

በቀጣይ ኢትዮጵያውያን እስረኞች ያሉበትን ሁኔታ በመለየት ከሚመለከታቸው የኢፌዲሪ መንግስት ባለድርሻ አካላት ጋር በመተባበር ወደ ሀገራቸው ለመመለስ እየሰራ ይገኛል።

Ethiopian Embassy in Kenya

Leave a Reply

Your email address will not be published. Required fields are marked *