ለድሬደዋ ከተማ ነዋሪዎች ስጋት እየሆነ የመጣው የጅብ መንጋ | OROMIYAA TIMES
Skip to toolbar

ለድሬደዋ ከተማ ነዋሪዎች ስጋት እየሆነ የመጣው የጅብ መንጋ

ለድሬደዋ ከተማ ነዋሪዎች ስጋት እየሆነ የመጣው የጅብ መንጋ

ለድሬደዋ ከተማ የገንደ ሮቃ አካባቢ ነዋሪዎች የጅብ መንጋ ስጋት እያሳደረባቸው መምጣቱ ተሰምቷል፡፡

ከቀድሞ ምድር ባቡር ድርጅት፣ ከጉምሩክና ከምስራቅ አየር ኃይል በተለምዶ ሰባተኛ ከሚባለው የጦር ካምፕ የሚዋሰነው ገንደ ሮቃ የሚባለው መንደር ከጊዜ ወደ ጊዜ በጥሻ እየተዋጠ በመምጣቱ የጅብ መንጋ የሚርመሰመስበት ስፍራ መሆኑን ነዋሪዎቹ አስረድተዋል።

በዚህ ስጋት ያደረባቸው ነዋሪዎች በአካባቢው የጅብ መንጋ ከጎሮው እየወጣ ነዋሪዎችን እንደሚተናኮል ነው የተገለፀው፡፡

በአንድ ወር ገዜ ውስጥ ብቻም ለአራተኛ ጊዜ መተናኮሉን ነው የሚናገሩት።

የጅብ መንጋው በአካባቢው እንዲርመሰመስ ካደረጉት ምክንያቶች መካከል ከምድር ባቡር ድርጅት የፍሳሽ ቱቦዎች፣ ከሰባተኛ ጦር ካምፕና ከጉምሩክ የሚጣሉ ተረፈ ምርቶች የሚለቃቅመው ምግብ ፍለጋ ነው ተብሏል።

ምግብ ፍለጋ የወጣው ጅብ መንጋም ባለፈው ቅዳሜ የአንድ 3 ዓመት ህፃን ህልፈት ምክንያት ሆኗል ነው የተባለው፡፡

መሰል ተመሳሳይ ጥፋት እንዳይከሰትም መንግስት አፋጣኝ መፍትሄ እንዲፈልግለት ነዋሪዎቹ ጠይቀዋል።

ምንጭ፡-ኢዜአ

Leave a Comment

Your email address will not be published. Required fields are marked *