የቻይና ተመራማሪዎች የኮሮናቫይረስን ውጤታማ በሆነ መንገድ ሊከላከሉ የሚችሉ ሁለት አዳዲስ መድኃኒቶችን አገኙ | OROMIYAA TIMES
Skip to toolbar

የቻይና ተመራማሪዎች የኮሮናቫይረስን ውጤታማ በሆነ መንገድ ሊከላከሉ የሚችሉ ሁለት አዳዲስ መድኃኒቶችን አገኙ

የቻይና ተመራማሪዎች የኮሮናቫይረስን ውጤታማ በሆነ መንገድ ሊከላከሉ የሚችሉ ሁለት አዳዲስ መድኃኒቶችን አገኙ

የቻይና ተመራማሪዎች የኮሮናቫይረስን ውጤታማ በሆነ መንገድ ሊከላከሉ የሚችሉ ሁለት አዳዲስ መድኃኒቶችን ማግኘታቸው እየተነገረ ነው።

አቢዶል እና ዳርናቪር የተባሉ መድኃኒቶች በቪትሮ ሴል ሙከራዎች ውስጥ ቫይረሱን ውጤታማ በሆነ መንገድ መከላከል እንደሚችሉ የዜዢያንግ ዩኒቨርሲቲ ፕሮፌሰር የሆኑት ሊ አመልክተዋል።

ከምስራቅ ቻይና ዜዢያንግ ግዛት የህክምና ባለሙያዎችን ወደ ማዕከላዊ ቻይና ሁቤይ ግዛት በማምጣት አዲስ የተያዙ በሽተኞችን የድንገተኛ ጊዜ ህክምና ለሻሻል ትልቅ ተስፋ ተጥሎበታል ነው የተባለው።

ሁለቱ አዲስ መድሃኒቶች በሀገሪቱ ብሔራዊ የጤና ኮሚሽን ሕክምና መርሃ-ግብር እንዲካተቱ ሐሳብ አቅርበዋል።

ከባለሙያወቹ አንዱ ቼን ዚንግ ሁለቱ መድኃኒቶች ያለ የሕክምና መመሪያ መወሰድ እንደሌለባቸውም አሳስበዋል።

ምንጭ፡-ሲጂቲኤን

Leave a Comment

Your email address will not be published. Required fields are marked *