የአፍሮ ጺዮን ኮንስትራክሽን ድርጅት ባለቤት 22 አካባቢ በተፈጠረው ግጭት ተጠርጥረው በቁጥጥር ሥር ዋሉ | OROMIYAA TIMES
Skip to toolbar

የአፍሮ ጺዮን ኮንስትራክሽን ድርጅት ባለቤት 22 አካባቢ በተፈጠረው ግጭት ተጠርጥረው በቁጥጥር ሥር ዋሉ

የአፍሮ ጺዮን ኮንስትራክሽን ድርጅት ባለቤት 22 አካባቢ በተፈጠረው ግጭት ተጠርጥረው በቁጥጥር ሥር ዋሉ

በአዲስ አበባ ከተማ 22 አካባቢ ቤተ ክርስቲያን ለመገንባት ከታጠረ ይዞታ ጋር በተገናኘ ጥር 26 ቀን 2012 ዓ.ም. ምሽት ላይ ለተፈጠረው ግጭትና ለሁለት ወጣቶች ሕይወት መጥፋት ምክንያት ሆነዋል የተባሉ ሰባት ተጠርጣሪዎችን ፖሊስ በቁጥጥር ሥር አዋላቸው:: ከነዚህም መካከል የአፍሮ ጺዮን ኮንስትራክሽን ባለቤት አቶ ሲሳይ ደስታ እንደሚገኙበት ምንጮች ገለጹ።

ከአፍሮ ጺዮን ኮንስትራክሽን ድርጅት ባለቤት በተጨማሪ ከኦርቶዶክስ ቤተ ክርስቲያን ዕውቅና ውጪ ፅላት የፈቀዱና መሬት እንዲያዝ ትዕዛዝ የሰጡ ሦስት ሰዎች፣ ከቦሌ ክፍለ ከተማ በጉዳዩ ላይ እጃቸው እንዳለበት የተጠረጠሩ ሁለት አመራሮችና የክፍለ ከተማው ደንብ ማስከበር ኃላፊ በቁጥጥር ሥር መዋላቸውን የሪፖርተር ምንጮች ገልጸዋል።

Ethiopian Reporter

Leave a Comment

Your email address will not be published. Required fields are marked *