የኦሮሚያ ቤተ ክህነት የኔ ነው ! ያንተ ነው! ያንቺ ነው! የኛ ነው! | OROMIYAA TIMES
Skip to toolbar

የኦሮሚያ ቤተ ክህነት የኔ ነው ! ያንተ ነው! ያንቺ ነው! የኛ ነው!

የኦሮሚያ ቤተ ክህነት የኔ ነው ! ያንተ ነው! ያንቺ ነው! የኛ ነው!

“የኦሮሚያ ቤተ ክህነት ይፈርሳል” ብለው ለሚቃዡ ሰዎችም እውነታውን አውቀውት ከወዲሁ እርማቸውን እንዲያወጡ ትንሽ ልበል። ዛሬ እኮ የትኛውም ዓለም ብትሄድ የኦሮሚያ ቤተ ክህነት ሴል (Cell) የሌለበት ክፍለ ዓለም የለም።ኦሮሚያ ውስጥ እያንዳንዱ ቀበሌ ድረስ ” እምቢ ለኦሮሚያ ቤተ ክህነት ” የሚሉ የኦሮሚያ ቤተ ክህነት አባላት አሉልህ።

ኢትዮጵያ ውስጥ ያለ የትኛውም የመንግስትም ሆነ የግል ድርጅት ውስጥ የማኅበሩ አባል የሌለበት የለም ። ከኢትዮጵያም ውጭ የኦሮሚያ ቤተ ክህነት ቅርንጫፍ የሌለበት ቦታ የለም። በተለይ በሰሜን አሜሪካ እና አውሮፓ።
ዛሬ ዛሬ በሰሜን አሜሪካና በአውሮፓ የሚደረጉ የኦሮሚያ ቤተ ክህነት እንቅስቃሴ ከሀገር ውስጡ የማይተናነሱ እየሆኑ ነው። በዓረቡ ዓለምና በዕሥያ ያለው የኦሮሚያ ቤተ ክህነት እድገትም ቀላል አይደለም። የትኛውም ክፍለ ዓለም ላይ የኦሮሚያ ቤተ ክርስትያን ጉዳይ የሚገደው በኦሮሚያ ቤተ ክርስትያን ጉዳይ ዝም የማይል የኦሮሚያ ቤተ ክህነት ሕዋስ አለ።

ባጭሩ የኦሮሚያ ቤተ ክህነት global ሆኗል። ወይ ደግሞ ነፋስ ሆኗል።አትይዘው አትጨብጠው። ነፋስ የማይነፍስበት ቦታ እንደሌለ ሁሉ የኦሮሚያ ቤተ ክህነት የሌለበት ቦታ የለም።ማን ነበር የኦሮሚያ ቤተ ክህነት የሃሳብ መስመር ( Imaginary line) ሆኗል ያለው።የኦሮሚያ ቤተ ክህነት ልዝጋው ብሎ የሚያስብ አላዊ እንኳን ቢመጣ ማጥፋት አይችልም:: ዋናው የኦሮሚያ ቤተ ክህነት ሥራ የሚሰራው በያንዳንዷ ደብር ፣ በየሰበካ ጉባኤው ፣ በየሰንበት ትቤቱ ፣ በየ አባላቱ ቤት ስለሆነ የኦሮሚያ ቤተ ክህነት ላይ የሚያመጣው ለውጥ insignificant ነው።

አሜሪካ ያለው የኦሮሚያ ቤተ ክህነት ብቻውን ሀገር ቤት ያለው የኦሮሚያ ቤተ ክህነት የሚሰራውን ሥራ የምስራት አቅም አለው። እድሜ ለኢንፎርሜሽን ቴክኖሎጂ ዛሬ አሜሪካ ሆነህ በያንዳንዱ ቀበሌ ፣በያንዳንዱ አጥቢያ ያለውን አባል ለቤተ ክርስትያን ሥራ ማስተባበር ከባድ አይደለም። It is a click or one call away. የኦሮሚያ ቤተ ክህነት በአንድ የጸሎት ቋንቋ የሚናገሩ ፣ በአንድ የእምነት ልብ የሚመሩ ፤ እንደ አንድ ቃል ተናገሪ እንደ አንድ ልብ መስካሪ የሆኑ በመቶ ሺህ የሚቆጠሩ ኦርቶክሳውያን ስብስብ ነውና እንዲህ በቀላሉ እንደ አንቧይ ካብ አትንደውም። ብትሰረስረውም መሰረቱ ጠንካራ አለት ነውና አታፈርሰውም። ከሁሉም በላይ የኦሮሚያ ቤተ ክህነት ጠባቂ ፈይሳ አዱኛና እመብርሃን ናትና ገና የኦሮሚያ ቤተ ክህነት ያድጋል። ይሰፋል።

Leave a Reply

Your email address will not be published. Required fields are marked *