በአምቦ ከተማ በተወረወረ ቦምብ 29 ሰዎች ቆሰሉ | OROMIYAA TIMES
Skip to toolbar

በአምቦ ከተማ በተወረወረ ቦምብ 29 ሰዎች ቆሰሉ

በአምቦ ከተማ በተወረወረ ቦምብ 29 ሰዎች ቆሰሉ

ዛሬ የካቲት 15/2012 ጠዋት በአምቦ ከተማ በተለምዶ ኮንዶሚኒየም አካባቢ ወይም አዲሱ መነናሃሪያ ተብሎ በሚታወቀው ቦታ ብልፅግና ፓርቲን ለመደገፍ በተካሄደ ሰልፍ በፈረሰኞች ላይ በተወረወረ ቦምብ 29 ሰዎች ቆሰሉ፡፡

ቦምቡ ከአዲስ አበባ ወደ አምቦ ከተማ መግቢያ አካባቢ እያለፉ የነበሩ ፈረሰኞችን ኢላማ ያድርግ እንጂ እነሱን የሚመለከት የከተማውን ነዋሪ ጨምሮ እንዳቆሰለ እና የተወሰኑ ፈረሰኞችም መጎዳታቸውን ነዋሪዎች ተናግረዋል፡፡

ነገር ግን ቦምቡ የመንገድ ዳር ቱቦ ውስጥ በመውደቁ ምክኒያት ያደረሰው ጉዳት ሊደርስ ከሚችለው ያነሰ መሆኑንም ጨምረው ተናግረዋል፡፡

Leave a Reply

Your email address will not be published. Required fields are marked *