የኢፌዴሪ አየር ኃይል ለከፍተኛ መኮንኖች ዛሬ ሹመት ይሰጣል | OROMIYAA TIMES
Skip to toolbar

የኢፌዴሪ አየር ኃይል ለከፍተኛ መኮንኖች ዛሬ ሹመት ይሰጣል

የኢፌዴሪ አየር ኃይል ለከፍተኛ መኮንኖች ዛሬ ሹመት ይሰጣል

በቢሾፍቱ በሚገኘው የኢፌዴሪ አየር ኃይል ጠቅላይ መምሪያ በዛሬው ዕለት 106 ለሚሆኑ ከፍተኛ መኮንኖች ሹመት እንደሚሰጥ ታውቋል።

በተጨማሪም በዛሬው ዕለት ላለፉት 6 ወራት በስልጠና ላይ የቆዩ የአየር ኃይል ወታደራዊ ፖሊስ አባላት ምረቃ እንደሚኖር ተገልጿል።
የኢፌዴሪ አየር ኃይል ዋና አዛዥ ሜጀር ጄነራል ይልማ መርዳሳ ሹመቱን እንደሚሰጡ ተጠቁሟል።

የኢፌዴሪ ጦር ኃይሎች ምክትል ኢታማዦር ሹም ጄነራል ብርሃኑ ጁላ በስፍራው ተገኝተው ንግግር ያደርጋሉ ተብሎ ይጠበቃል።
ባለፉት 6 ወራት በተቋሙ ከፍተኛ አፈፃፀም ላስመዘገቡ ሰራተኞችም ሽልማት እንደሚበረከትለት(ኢቢሲ)ዘግቧል።

Toleeraa Caalaa

Leave a Comment

Your email address will not be published. Required fields are marked *